Fana: At a Speed of Life!

የነዳጅ ስርጭትና አቅርቦቱ ላይ ምንም አይነት ችግር አለመኖሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅ ስርጭት እና አቅርቦቱ ላይ ምንም አይነት ችግር የለም ሲል የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ሀይለማሪያም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ‘’ነዳጅ የለም’’ በሚል እየተናፈሰ ባለው ወሬ ተሽከርካሪዎች በማደያዎች ነዳጅ ለመቅዳት የሚያደርጉት ረዣዥም ሰልፎች ከእውነታው ጋር የተቃረነ ተግባር ነው።

አለ የሚባለው ችግር ለእኛም ግልጽ አይደለም ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ፥ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የነዳጅ ስርጭት ጊዜውን ጠብቆ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ለአለብነትም ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም በየቀኑ በአማካይ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ሊትር ነዳጅ የተሰራጨ ሲሆን ፥ ትናንትና ብቻ 3 ሚሊየን ሊትር ነዳጅ ወደ ገበያ መሰራጨቱን አንስተዋል።

ሆኖም በየወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ጋር ተያይዞ ‘‘የዋጋ ልዩነት ይኖራል’’ በሚል ተሽከርካሪዎች በማደያዎች መሰለፋቸው ከዚህ ቀደም ከሚፈጠረው ሁኔታ መገመት ይቻላልም ነው ያሉት።

አንዳንድ አሽከርካሪዎችም በነዳጅ ማደያዎች ተሸከርካሪዎች በመሰለፋቸው ብቻ ነዳጅ የሌለ መስሏቸው የሚሰለፉ እንዳሉም ነው የጠቀሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለስርጭት እየቀረበ ያለው ነዳጅ በመጠኑ እየጨመረ ከመምጣት ውጪ ቅናሽ የታየበት አይደለም ያሉትአቶ ታደሰ ፥ በመሆኑም ህብረተሰቡ በሚናፈሱ ወሬዎች ሊታለል አይገባም ብለዋል።

በበላይ ተስፋዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.