በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ5 ሺህ በላይ ሴቶች በማህጸን ጫፍ ካንሰር ለህልፈት ይዳረጋሉ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ5 ሺህ በላይ ሴቶች በማህጸን ጫፍ ካንሰር በሽታ ለህልፈት እንደሚዳረጉ ተገለጸ።
የማህጸን ጫፍ ካንሰርን በተመለከተ የዘርፉ ምሁራን የጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት የተሳተፉበት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ በሽታው ይዟቸው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ታማሚዎቹ ወደ ህክምና ጣቢያ መምጣታቸው የበሽታውን አስከፊነት እንዳባባሰው ተገልጿል።
ለዚህም የግንዛቤ ማነስ፣ በዘርፉ ላይ የሚታየው የህክምና እጥረት እንዲሁም ለምርምር ስራዎች በቂ ድጋፍ አለመደረጉ በሽታውን በሚፈለገው ልክ መከላከል እንዳይቻል ማድረጉ ተጠቅሷል።
በበሽታው ለህልፈት ከሚዳረጉት ባለፈም በየአመቱ 7 ሺህ አዳዲስ ህሙሟን እንደሚመዘገቡ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
የጤና ሚኒስቴርን በመወከል በመድረኩ የተገኙት ዶክተር ካሳሁን ተስፋዬ፥ በሽታውን ለመከላከል እና በዘርፉ ላይ ለሚደረገው ምርምር የሚውል 4 ሚሊየን ብር መመደቡን ተናግረዋል።
ውይይቱ ለቀጣይ ሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision