ድንበር ተሻጋሪ የጋራ የበሽታዎች ቁጥጥር ላይ የጋራ ግምገማ በመካሄድ ላይ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ድንበር ተሻጋሪ የጋራ በሽታዎች ቁጥጥር ላይ የጋራ ግምገማ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው።
ግምገማው ትኩረት በሚሹ የቆላ በሽታዎች ኦንኮሰርኪያሲስ እና ተላላፊ የዝሆኔ በሽታዎች ላይ ድንበር ተሻጋሪ የጋራ በሽታዎች ቁጥጥር ላይ ነው እየተካሄደ ያለው።
በጉባኤው ኢትዮጵያን ጨምሮ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተወያዩ መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።