Fana: At a Speed of Life!

በጃፓኗ ዳይመንድ ፕሪንስ መርከብ ተለይተው የቆዩ 600 ሰዎች መርከቧን ለቀው ወጡ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ለቀናት በጃፓኗ በዳይመንድ ፕሪንስ መርከብ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ተለይተው የቆዩ 600 ሰዎች መርከቧን ለቀው ወጥተዋል።

3 ሺህ 700 መንገደኞችን አሳፍራ የነበረችው ዳይመንድ ፕሪንስ መርከብ ከሁለት ሳምንት በላይ በዮኮሀማ ወደብ ቆይታለች።

በመርከቧ የነበሩት ተሳፋሪወች በጃፓን የጤና ጥበቃ አገልግሎት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።

ባለፈው ሰኞ ከ300 በላይ አሜሪካውያን በሁለት በረራዎች ወደ አሜሪካ መግባታቸው የሚታወስ ነው።

በዛሬው ዕለትም ከ106 የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች መካከል የተወሰኑት ሆንግ ኮንግ ገብተዋል።

የካናዳ መንግስት በበኩሉ ዜጎቹን እያስወጣ ሲሆን፥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በጃፓን ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚቆዩ አስታውቋል።

በመርከቧ 251 ካናዳውያን የሚገኙ ሲሆን፥ 47 የሚሆኑት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ተብሏል።

የጃፓን መንግስት በበኩሉ በመርከቧ 79 አዲስ የቫይረሱ ተጠቂወች መገኘታቸውን ገልጿል፥ ይህም ከቻይና ውጭ የቫይረሱን ተጠቂዎች ቁጥር ወደ 620 ከፍ አድርጎታል ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.