Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከኔዘርላንድስ የውጭ ንግድ እና የልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኔዘርላንድስ የውጭ ንግድ እና የልማት ትብብር ሚኒስትር ሲግሪድ ካግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት የትብብር መስኮች ዙሪያ መምከራቸው ነው የተገለጸው።

ኔዘርላንድስ በግብርና እና በውሃ መስኮች ያላትን ከፍተኛ ልምድ ለኢትዮጵያ ማካፈል እንደምትፈልግ ሲግሪድ ካግ ተናግረዋል፡፡

ኔዘርላንድስ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመንና ውጤታማ ውሃ አጠቃቀምን ማዳበር የሚያስችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗንም ነው ያመለከቱት፡፡

ግብርናውን በማሳደግ በኢኮኖሚው ላይ እምርታ ማምጣት የኢትዮጵያ መንግስት ግንባር ቀደም አጀንዳዎች መሆናቸውን ያስታወሱት ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ፥ለዚህ ስኬታማነትም ከኔዘርላንድስ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ከሆኑት ክሪሱላ ዛካሮፑሉ ጋር ተወያይተዋለ።

በዚህም የአውሮፓ ህብረት በአህጉራዊ ደረጃ ሊሰጥ በሚችልባቸው በስርዓተ ጾታና በሌሎች የትብብር ዘርፎች ዙሪያ መምከራቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.