Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ሕንጻ የፊታችን እሁድ ይመረቃል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ሕንጻ የፊታችን እሁድ እንደሚመረቅ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ገለጹ፡፡
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ80 ዓመት የምስረታ በዓሉንና የዋና መስሪያ ቤት የህንፃ ምረቃን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
 
መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ፥ “በምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የሆነውን ይህን ህንፃ ምረቃ ከ80 ዓመት ልደታችን ጋር በመገናኘቱ አስደሳች ነው” ብለዋል፡፡
ከመሬት በላይ 209 ነጥብ 15 ሜትር ከፍታ ያለው ህንፃው ፥ ባለ 53 ወለል ነው።
 
በውስጡም የቢሮ አገልግሎት ከሚሰጡ ክፍሎች በተጨማሪ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን፣ ሙዚየም እና ሲኒማ ቤትን ያካተተ ሲሆን፥ እስከ 1 ሺህ 500 መኪናዎችን መያዝ የሚችል ማቆሚያም አለው።
 
ግንባታው 5 አመት ከ11 ወር የወሰደ ሲሆን፥ 303 ሚሊየን 500 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጭ እንደተደረገበት አቶ አቤ ሳኖ አብራርተዋል፡፡
 
ባንኩ ባሳለፋቸው አመታት ለሌሎች ባንኮች መመስረት አስተዋፅኦ እንደነበረውም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
 
በፈቲያ አብደላ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.