Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ልማት ባንክና መድን ድርጅት በግማሽ ዓመቱ  10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር አተረፉ  

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በግማሽ በጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘታቸው ተነገረ።

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ድርጅቶቹ አቅደውት ከነበረው 9 ነጥብ 67 ቢሊየን ብር ትርፍ አንጻር ሲታይ ክንውናቸው ከዕቅዳቸው በ11 በመቶ ብልጫ አሳይቷል።

በዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 9 ነጥብ 33 ቢሊየን ብር በማትረፍ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአጠቃላይ በስድስት ወሩ 951 ነጥብ 6 ሚሊየን ሊያተርፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ደግሞ 427 ነጥብ 89 ሚሊየን ብር ወይም የዕቅዱን 101 አትርፎ ለዘርፉ ትርፍ አፈጻጸም የ4 በመቶ ድርሻ አበርክቷል ተብሏል፡፡

ድርጅቶቹ ከሰጡት የባንክና የመድን አገልግሎቶች ትርፉን ማግኘታቸውም ነው የተገለጸው።

 

በታሪክ አዱኛ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.