Fana: At a Speed of Life!

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም መካሄድ ይጀምራሉ፡፡

በዚህ መሰረትም ፋሲል ከነማ እና አዳማ ከተማ ቀን 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል፡፡

የባለፈው ዓመት ሻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ በጊዜያዊነት ሊጉን መምራት የሚያስችለውን ውጤት ለማግኘት አዳማን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

በአንፃሩ አዳማ ከተማ ደረጃውን ለማሻሻል ወደ ሜዳ ይገባል ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡

በፋሲል ከነማ በኩል የቡድኑ አምበል ያሬድ ባየ ከጉዳት መልስ በጨዋታው የሚሰለፍ ሲሆን÷ አማካዩ በዛብህ መለዮ በጉዳት ምክንያት እንደማይሰለፍ ተገልጿል፡፡

ጨዋታውን ሄኖክ አክሊሉ በዋና ዳኝነት እንደሚመሩት ተጠቁሟል፡፡

ፕሪምየር ሊጉ ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ሀዲያ ሆሳና ከሰበታ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ከወራጅ ቀጠና በሁለት ነጥብ ርቆ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳና ከ 4 ጨዋታ የድል ጉዙ በኋላ በጅማ አባ ጅፋር 4 ለ 2 መሸነፉ ሚታወስ ሲሆን÷ ሰበታ ከነማ ደግሞ ከ 3 ጨዋታ ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ነው ዛሬ ከነብሮቹ ጋር ጨዋታውን የሚያደርገው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.