የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን በነገው ዕለት ያካሂዳል።
የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት የፕሬስና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም እንቻለው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ምክር ቤቱ በጉባኤው የአስተዳደሩን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምን ይገመገማል ብለዋል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች የ6 ወራት አፈጻጸም፣ የመሬት ይዞታ ማስለቀቅ እና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ ተወያይቶ ማጽደቅ እንዲሁም ልዩ ልዩ ሹመቶችን ማጽደቅ የምክር ቤቱ አጀንዳዎች መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!