በጦርነቱ የተጎዱ ከተሞችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ የተጎዱ ከተሞችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም በትኩረት እንደሚሰራ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሚኒስቴሩ የመኖሪያ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አዘጋጅነት÷ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎች የመጠለያ ቤቶች ልማት ሁኔታ ላይ ከዩ ኤን ሀቢታት እና ከክልሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመኖሪያ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ታደሰ ከበበ ፥ በጦርነቱ ለተጎዱ ከተሞች በተናጠል ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎችና የጉዳቱን ደረጃ በመለየት ከጦርነቱ ነጻ በሆኑ አካባቢዎች ላይ በዘላቂነትና በተሻለ መንገድ ለመስራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በየሙያ ዘርፉና ካለው አቅም አንጻር ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
በመድረኩ በቀረቡት ሰነዶች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግና ለተነሱት አስተያየቶችና ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የጋራ አቋም በመያዝ የውይይት መድረኩ መጠናቀቁንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!