Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን በቁሳቁስና በመልሶ ግንባታ ለመደገፍ ከዩኒሴፍ ጋር ተስማማ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስቴር በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን በቁሳቁስና መልሶ ግንባታ ለመደገፍ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር ተስማምቷል፡፡

የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድና የህፃናት ድጋፍ አገልግሎትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የህፃናት ጥበቃ ኃላፊና ባለሙያዎች ጋር በሚኒስትር ዴኤታዋ ቢሮ በተለያዩ የህፃናት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በዚህም የህፃናት ጥበቃ ጉዳይ አያያዝ ስርዓት ማዕቀፍን ከሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር ማዕቀፉን ተግባራዊ ለማድረግ የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል፡፡

በጉዳይ አያያዝ ስርዓት የሚያልፉ ህፃናት የመረጃ አያያዝ ስርዓት፣በዲጂታል ለማስጀመርና በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን በቁሳቁስና መልሶ ግንባታ ለመደገፍ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

በተጨማሪም በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊትን ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የዩኒሴፍ ተወካይ ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ በህፃናት ላይ በበይነ መረብ የሚፈፀሙ ጾታዊ ጥቃቶችን ለማስቆም የሚያግዝ የፕሮጀክት ፈንድ ኢትዮጵያ እንድትመረጥ ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ላደረገው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም ተቋማቱ ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው በውይይቱ ላይ መነሳቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.