የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአበባ ምርቶችን ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት እያጓጓዘ መሆኑን አስታወቀ

By Meseret Awoke

February 09, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የፍቅረኞች ቀን’ በሚውልበት በዚህ ወር የአበባ ምርቶችን ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት እያጓጓዘ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወር ወደ 95 ሚሊየን የሚጠጋ አበባ ማጓጓዙን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ “የፍቅረኞች ቀን” (የቫለንታይን ደይ) በሚውልበት በዚህ ወር የሙቀት መቆጣጠሪያ በተገጠመላቸው ዘመናዊ እቃ ጫኝ አውሮፕላኖቹ የአበባ ምርቶችን ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት በማጓጓዝ ላይ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!