የሀገር ውስጥ ዜና

በእነ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) የክስ መዝገብ ተከሣሾች አቅርበውት የነበረው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

By Feven Bishaw

February 10, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አብዲ መሐመድን ጨምሮ 17 ተከሣሾች የሌሎች ክስ ተቋርጦ የኛ ክርክር የሚቀጥልበት ምክንያት የለም በሚል ባሳለፍነው ማክሰኞ የካቲት 01 ቀን 2014 ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደረገ፡፡

ተከሣሾቹ ከዚህ በኋላ በሚኖር ቀጠሮ ፍርድ ቤት አንቀርብም ባሉት መሰረት 14ቱ ዛሬ ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡