Fana: At a Speed of Life!

የሚፈጠሩ ዕድሎችን ወጣቶች በአግባቡ ሊጠቀሙባቸው እንደሚገባ ሚኒስቴሩ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚፈጠሩ ዕድሎችን ወጣቶች በአግባቡ ሊጠቀሙባቸው እንደሚገባ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።
ሥራ ፈጣሪዎችን ከኢንቨስተሮች ጋር የሚያገናኝ ዲጂታል መተግበሪያ ይፋ የተደረገ ሲሆን÷ ወጣቶች የሚፈጠሩ ዕድሎችን በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባ ተገልጿል።
በወጣቶች የተቋቋመው እና ስሙኒ የተባለው ድርጅት ከኮካኮላ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር 10 በጅምር ያሉ የስራ ሃሳቦችን በፋይናንስ ሊደግፍ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በግሉ ዘርፍ የሚፈጠሩ ስራዎች ሊበረታቱ እንደሚገባ እና ወጣቶች የሚፈጠሩ ዕድሎችን በአግባቡ ሊጠቀሙባቸው ይገባል ሲሉ በሚኒስቴሩ የአጋርነትና ፈንድ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ጥዑመዝጊ በርሔ ተናግረዋል፡፡
መተግበሪያውን ያዘጋጀው ድርጅት መስራች ወጣት ብሩክ ግርማ፥ በመተግበሪያው እኔ ይገጥሙኝ የነበሩ አስቸጋሪ የሆኑ የፋይናንስ እጥረትና ሌሎቹንም ያቃልላል፤ ውጤታማ ትብብርም ይፈጥራል ብሏል።
በመተግበሪያው በመታገዘ በአንድ ዓመት ውስጥ 10 ሺህ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን ከኢንቨስተሮች ጋር ለማገናኘት ማቀዱንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኮካኮላ ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ ዳረል ዊልሰን በበኩላቸው፥ ኩባንያው ወጣቶችን በተለይም ሴቶችን በመደገፍ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.