Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኅብረቱ ጉባዔ በመልካም ሁኔታ እንዲካሄድ የጸጥታው ዘርፍ ላደረገው አስተዋጽዖ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ኅብረት 35ኛ መደበኛ የመሪዎች ጉባዔ በመልካም ሁኔታ እንዲካሄድ የጸጥታው ዘርፍ ላደረገው ብርቱ አስተዋጽዖ ምስጋና አቀረቡ፡፡

የኢፌዴሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የምስጋና መርሀ-ግብር እያካሄደ ነው።
የጋራ ግብረ-ኃይሉ በሀገራችን የተካሄዱ አህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ሁነቶች ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ የተለያዩ አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው ምስጋና እያቀረበ የሚገኘው።
ምስጋና የቀረበላቸው፥ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ፣ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሀይል እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አግልግሎት መሆናቸውም ተገልጿል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢፌዴሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አመራሮች እና አባላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን÷ “የኢትዮጵያ የፀጥታ አካላት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ኩራት መሆናችሁን በተግባር ስላረጋገጠችሁ ብዙ የአፍሪካ መሪዎች ኮርተውባችኋል”ብለዋል።
በዚህ የምስጋና ስነ ስርዓት ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ የደህንነት ተቋማት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.