Fana: At a Speed of Life!

በሁሉም ግንባሮች ኢትዮጵያዊ አንድነትን ጠብቆና አጥብቆ መጓዝ ተደማጭነትን ያረጋግጣል- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሱ ውጫዊ ጫናዎችን በአንድነት ከመመከት ባሻገር በብሄራዊ ደረጃ የተጀመረውን ዘላቂ ሰላም እና ዕድገት የማረጋገጥ ጥረት በህብረት መደገፍ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ፥ የ”በቃ” ዓለምአቀፍ ንቅናቄን በማስተባበር በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀሰው “የሰላምና አንድነት ግብረሃይል” አመራሮች እና አባላትን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ ላይ የውጪ ሃይሎች ሃገር ውስጥ ካሉ የጥፋት ቡድኖች ጋር ጥምረት በመፍጠር ኢትዮጵያን ለማፍረስ በተለያዩ ግንባሮች የከፋ ጥፋት በመፈፀም እና የከረረ ጫና በመፍጠር የሃገርን ልዑዓላዊነትን ሲፈታተኑ እንደነበር አቶ ደመቀ አስታውሰዋል።

በተለይ በውጪ ሃይሎች የሚወሰዱት ፍትሃዊነት የጎደላቸው እርምጃዎች የኢትዮጵያን ልዑዓላዊነት በእጅጉ እንደተፈታተኑ በመጥቀስ ፥ ውጫዊ ጫናዎችን የመመከት ተልዕኮ ራሱን የቻለ ፈታኝ ግንባር እንደነበር ተናግረዋል።

ውጫዊ ጫናዎች በሚመከቱበት ግንባር በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በ”በቃ” የንቅናቄ መርህ በዓለም አደባባይ ለሃገራቸው ፍትህን በመሻት ድምፃቸውን በስፋት አስተጋብተዋል።

በተመሳሳይ በሰሜን አሜሪካ የ”በቃ” ንቅናቄን በማስተባበር እና በመምራት “የሰላምና አንድነት ግብረሃይል” አመራሮች እና አባላት የዚህ ታሪካዊ ዘመቻ አካል በመሆን ላበረከቱት አስተዋፅዖ አቶ ደመቀ አመስግነዋል።

በሁሉም ግንባሮች ኢትዮጵያዊ አንድነት ጠብቆ እና አጥብቆ መጓዝ ተደማጭነትን ከማረጋገጡ ባሻገር ትርጉም አዘል ድሎችን ለማስመዝገብ እንደሚያግዝ ከዓለምአቀፍ ንቅናቄው ቋሚ ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል ነው ያሉት።

በሃገር አቀፍ ደረጃ መንግስት ዘላቂ ሰላም እና ዕድገት ለማረጋገጥ ተስፋ ሰጪ እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመሩን በዝርዝር አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሱ ውጫዊ ጫናዎችን በአንድነት ከመመከት ባሻገር በብሄራዊ ደረጃ የተጀመረውን ዘላቂ ሰላም እና ዕድገት የማረጋገጥ ጥረት በህብረት መደገፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.