Fana: At a Speed of Life!

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከነገ ጀምሮ ተማሪዎችን እንደሚቀበል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ነገ እና ከነገ በስቲያ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን እንደሚቀበል አስታወቀ፡፡

በዩኒቨርሲቲው መደበኛውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስጀመር በዝግጅት ምዕራፍ ዙሪያ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ፥ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አመራሮች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀጃው ደማሙ ኢትዮጵያ በገጠማት ችግር ምክንያት መደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት ወቅቱን ጠብቆ አለመጀመሩን ጠቅሰው ፥ በአሁኑ ወቅት ትምህርት ለማስጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ከየካቲት 05-06/2014 ዓ/ም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ቅበላ ይደረጋልም ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ፥ የዘገየውን የመማር ማስተማር ሂደት በአጭር ጊዜና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲሸፈን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ በአግባቡ እንዲወጣ መልዕክት አስተላፈዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ያላለም ፈንታሁን በበኩላቸው ፥ ዩኒቨርሲቲው አሸባሪ ቡድኑ ደባርቅን ይዣለሁ በሚልበት ወቅት ተማሪዎቹን አስመርቋል ፤ በፈተና ውስጥም ሆኖ በርካታ ሀገራዊ ችግር ፈቺ ስራዎችን ፈፅሟል ብለዋል፡፡

ስለሆነም ውጤታማ ተማሪዎችን እንዲያፈራ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከምንጊዜውም በላይ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማሳሰባቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.