የመዲናዋ ነዋሪዎች በጦርነቱ ለተጎዱ ትምህርት ተቋማት የሚሆን ድጋፍ እያደረጉ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የያዘው እቅድ አካል የሆነው የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ በተቋሙ መግቢያ 4ኪሎ አደባባይ ፊት ለፊት እየተካሄደ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለወደሙ ትምህርት ተቋማት የሚሆን የደብተር፣ እስክርቢቶ፣ መርጃ መፀሐፍት እና ለነዋሪዎች የሚሆን የአልባሳት ድጋፍ በቦታው በመገኘት እያበረከቱ ነው።
ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻውም ለሁለት ሳምንታት እንደሚቀጥል ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም በአጭር የፅሁፍ መልዕክት 9222 ላይም ማህበረሰቡ የሚፈልገውን የብር መጠን በቁጥር እየፃፈ በመላክ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራም ተጀምሯል።
ህብረተሰቡም የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን እንቅስቃሴ በቻለው አቅም እንዲደግፍ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!