የሀገር ውስጥ ዜና

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ ያስችላል – አቶ ደስታ ሌዳሞ

By Meseret Awoke

February 11, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥና የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል እንደሚያስችል የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንቅስቃሴ በመስክ እየጎበኙ ነው።

በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ በ108 ሄክታር ላይ እየለማ የሚገኘውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በመጎብኘት ላይ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር የውሀ ሀብቶቻችንን ከሰው ኃይላችን ጋር በማቀናጀት ልማቱን ማስፋፋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ልማቱ እንደ ክልል ብሎም እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥና የዜጎችን ሕይወት ትርጉም ባለው መልኩ ለማሻሻል ያስችላልም ነው ያሉት ።

በክልሉ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተከናወነ ያለው በሙከራ ደረጃ መሆኑ ተነስቷል።

በመስክ ገብኝቱ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊን አቶ መስፍን ቃሬን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ የዘገበው ኢዜአ ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!