Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 6 ወራት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች ከ104 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች ከ104 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

የኮርፖሬሽኑ የማርኬቲንግ እና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሄኖክ አስራት የተቋሙን የ6 ወራት ስራ አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ ኢትዮጵያ በችግር ውስጥ ብትሆንም በፓርኮቹ ሰፊ ስራዎችን በመስራት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት የተሻለ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 25 በመቶ እድገት አሳይቷል ነው ያሉት፡፡

80 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ ከውጭ የሚገቡ ተተኪ ምርቶችን በፓርኮቹ በማምረት ለገበያ ማቅረብ መቻሉም ተመላክቷል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ከ 33 ሺኅ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ያሉት ኃላፊ÷ ሁለት ትልልቅ ባለሃብቶች ቦሌ ለሚ እና ድሬደዋ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ወደ ስራ ይገባሉ ብለዋል።

በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጉዳት የደረሰበት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ መግባቱን እና ምርቶችን ወደ ውጪመላክ መጀመሩም በመግለጫው ተነስቷል።

የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ አሁን ላይ 97 በመቶ መድረሱም ተመላክቷል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የፕላኒግ መምሪያ ሃላፊ አቶ ፀጋዬ ዘካሪያስ የወሰን ማስከበር ጥያቄዎች፣የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ፣የሲሚንቶ እጥረት በገበያ ላይ መከሰቱ ተግዳሮቶች ናቸው ብለዋል።

ኮርፖሬሽኑ በግማሽ በጀት ዓመቱ 32 ሚሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱንም ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ዙፋን ካሳሁን እና ቅድስት ብርሃኑ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.