የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አሶሳ ከተማ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ገቡ።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ አሶሳ ህዳሴ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰንን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በቆይታቸውም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ ክልል የጋራ የሰላምና የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚያስገነባው ትምህርት ቤት ግንባታውን ያስጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!