Fana: At a Speed of Life!

የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ስራ በመከናወኑ ሰላማዊ ክልል መፍጠር ተችሏል – አቶ እርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝቡን የቆዩ እሴቶች በመጠቀም የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ስራ በመከናወኑ በተነጻጻሪ ሲታይ ሰላማዊ ክልል መፍጠር እንደተቻለ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ተናግረዋል።

የደቡብ ክልል መንግስት የ2014 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው ፡፡

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ መድረኩን ሲያስጀምሩ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፥ እንደ ሀገር ያጋጠመውን የህልውና አደጋ ለመመከት የክልሉ ህዝብ ያደረገው አጠቃላይ ድጋፍ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ እንደሆነ በማንሳት ለህዝቡና ለአመራሩ ምስጋና አቅርበዋል።

የህዝቡን የቆዩ እሴቶች በመጠቀም የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ስራ በመሰራቱ በተነጻጻሪ ሲታይ ሰላማዊ ክልል መፍጠር እንደተቻለ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት የተለያዩ የልማት ስራ ግቦችን በበጀት ዓመቱ አስቀምጦ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን አስታውሰው ፥ በዕቅዱ አፈጻጸም ሰፊ ውይይት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩም የገጠር ልማት ዘርፍ፣ የመሰረተ ልማት፣ የከተማ ልማት፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የሪፎርምና የመልካም አስተዳደር ክላስተር የበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸማቸው ቀርቦ ሰፊ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ የስራ ሃላፊዎች የተቋማቸውን የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት እያቀረቡ እንደሚገኙ ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.