Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚያስገነባው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ወረዳ ባሮ ቀበሌ ለሚያስገነባው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀመረ፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን የአዳሪ ትምህርት ቤቱን ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡ ሲሆን፣ የግንባታ ስራውንም አስጀምረዋል።
በ79 ሚሊየን ብር የሚገነባው አዳሪ ትምህርት ቤቱ የግንባታው ወጪ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጀት የሚሸፈን መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሁለቱን ክልሎች ሕዝቦች ሠላም እና ልማት የበለጠ ለማጠናከር የተጀመሩ የጋራ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም የሁለቱ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.