Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የከፋ የድርቅ ጉዳት ለታየባቸው 15 ወረዳዎች ከ255 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የከፋ የድርቅ ጉዳት ለታየባቸው 15 ወረዳዎች ከ 255 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአሁኑ ወቅት እንደ ክልል በተከሰተው የድርቅ ምክንያት የከፋ ሁነትና ጉዳት ለታየባቸው በስድስት ዞኖች 15 ወረዳዎች 62 ሺህ 336 የቤተሰብ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ እና ድጋፉ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል ።

የሶማሌ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሙሁየዲን አብዲ በሰጡት መግለጫ ፥ የሶማሌ ክልል መንግስት እስከ አሁን ድርቁ በአርብቶ አደሩና እንስሳቱ ህይወት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በ9 ዞኖች በ78 ወረዳዎች ላይ የመጠጥ ውሀ ፣ የእንስሳት መኖና የምግብ እሬሽኖችን እያዳረሰ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አሁን ላይ ለ62 ሺህ 336 አባወራ ቤተሰብ እየተደረገ ያለው የገንዘብ ድጋፍ መጠነኛ ኢኮኖሚያዊ አቅም እንዲሆናቸው ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል ።

አቶ ሙህየዲን አክለውም ፥ አሁን ላይ የክልሉ መንግስት የካፒታል የልማት ስራዎችን በማቆም የአርብቶ አደሩን ህይወትና እንስሳት የመታደግ ሙሉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡

በቀጣይም የኑሮ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆነ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ፕሮግራም ከክልሉ እርሻ ቢሮ ጋር በመሆን 500 ሚሊየን ብር የመደገፍ ስራ ይኖራል ብለዋል ።

ድርቁን በመከላከል ረገድ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የክልሉ መንግስት እያደረገ ካለው ዘርፈ ብዙ ጥረት የተለያዩ አጋር አካላትና የተለያዩ ክልሎች እያደረጉ ያሉት የገንዘብና የአይነት ድጋፎች የሚበረታቱ መሆኑን ም አንስተዋል፡፡

ከድርቁ ስፋት ጋር ተያይዞ በተጠና ጥናት አጠቃላይ ወደ 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ማስታወቃቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.