Fana: At a Speed of Life!

የተሻሻለ የምጥን መኖ አዘገጃጀት በአርሶ አደሩ ጓሮ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት መኖን ንጥረ ነገር ይዘት ለማሻሻል እያደረገ ባለው ጥረት የምጥን መኖ አዘገጃጀት በአርሶ አደሩ ጓሮ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገለጸ።
የምጥን መኖ አዘገጃጀትን በተመለከተ ከ30 ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ለተውጣጡ የመኖ ልማት ባለሙያዎች በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ባለሙያዎቹ የምጥን መኖ አዘገጃጀት በየአካባቢው እያንዳንዳቸው ለ10 አርሶ አደሮች በተግባር ሰርተው እያሳዩ ሲሆን÷ እያንዳንዱ ሰልጣኝ አርሶ አደርም በየአካባቢው ከ10 እስከ 15 ለሚሆኑ አርሶ አደሮች በጓሯቸው ተግባራዊ የምጥን መኖ ዝግጅት ተሞክሮ እያሰፉ መሆኑን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህ ተግባራዊ የምጥን መኖ አዘገጃጀት በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ (ወህኒ ቀበሌ) እና ባህር ዳር ዙሪያ (ሮቢት ቀበሌ) በአርሶ አደሩ ጓሮ በይፋ ተጀምሯል።
ግብርና ሚኒስቴር ለምጥን መኖ ዝግጅት የሚሆኑ አስፈላጊ ግብዓቶችን ለቀበሌዎች ያቀረበ ሲሆን÷ ተግባራዊነቱንም በቅርበት ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር መኖ ልማት ዳይሬክተር አቶ አለሙ ወልዴ በአማራ ክልል ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ተገኝተው የተሻሻለ ምጥን የመኖ አዘገጃጀት አተገባበርን በተመለከተ እንደገለጹት÷ ሚኒስቴሩ የተሻሻለ ምጥን የመኖ ማዘጋጃ ግብዓቶችን (ቴክኖሎጂዎችን) በተመረጡ ቀበሌዎች በአርሶ አደሩ ጓሮ ተደራሽ እያደረገ መሆኑንና ለዚህም የድጋፍ እና ክትትል ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.