የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ጤና ድርጅት የመጀመሪያውን 10 ሜትሪክ ቶን የመድሐኒት እና የሕክምና ቁሳቁሶች አቅርቦት መቀሌ አደረሰ

By Alemayehu Geremew

February 11, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ከ33 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የመድሐኒት እና የሕክምና ቁሳቁሶች አቅርቦት ውስጥ የመጀመሪያውን 10 ሜትሪክ ቶን ወደ ትግራይ ማድረሱን ገለጸ፡፡

አቅርቦቱ በተባበሩት መንግስታቱ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ጫኝ አውሮፕላን የሁለት ጊዜ በረራ ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ መድረሱንም ነው በኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት በትዊተር ገጹ ያስታወቀው፡፡

በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናትም በተከታታይ በረራዎች ቀሪው አቅርቦት እንደሚሰራጭ ተመልክቷል፡፡