Fana: At a Speed of Life!

ከ106 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው ሳምንት ከ106 ሚሊየን 170 ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል ነው 92 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 13 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የተያዙት፡፡

የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ የመዋቢያ እቃዎች ፣የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ድሬድዋ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መሆናቸውን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮሚሽኑ የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸምን ለመከላከል ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.