Fana: At a Speed of Life!

የአውራምባ ማህበረሰብ 50ኛ አመት በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውራምባ ማህበረሰብ 50ኛ አመት በዓል “ኑ ጠቃሚ እሴቶቻችንን በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የማህበረሰቡ መስራች የክብር ዶክተር ዙምራ፥ ጠብን ከማብዛት ይልቅ ፍቅርን እየዘሩ መኖር ያስፈልጋል ብለዋል።

የሰው ልጆችን ጉዳት በመረዳት መኖር እንደሚያስፈልግ ገልጸው፥ የወገኑን ችግር የማይረዳ ሰው ከእንስሳት ተለይቶ ሊታሰብ አይገባውም ነው ያሉት።

መጥፎ አመለካከትን በማስተካከል ለቀጣይ ትውልድ በጎነትን ማውረስ ይገባል ያሉት ደግሞ የክብር ዶክተር ዙምራ ባለቤት ወይዘሮ እናነይ ክብረት ናቸው።

ወይዘሮ እናነይ የማህበረሰቡን መልካም እሴት ለማስቀጠል እርሳቸውና ባለቤታቸው የሚበሉትን እስከመቸገር የደረሱበት ወቅት እንደነበርም ማስታወሳቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

የአውራምባ ማህበረሰብ እምነቱ ስር መለያው አንድነት ሆኖ ለ50 ዓመታት በስኬት ማሳለፉን በመድረኩ ተገልጿል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.