የሀገር ውስጥ ዜና

የአካባቢን ሥነ-ምኅዳር መሠረት ያደረጉ የሰብል ዓይነቶችን በስፋት ማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

By Feven Bishaw

February 12, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካባቢን ሥነ-ምኅዳር መሠረት ያደረጉ የሰብል ዓይነቶችን በስፋትና በጥራት እንዲመረቱ ማስቻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ከውጭ የሚገባ ምርትን ለመተካት እና ገቢን ለማሣደግ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችን ማሳ የጎበኙ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በጅማ ዞን እና ከተማ ዙሪያ በመልማት ላይ የሚገኙ የቡና እና የበጋ የመስኖ ስንዴ ኩታ ገጠም እርሻዎች ምርት አበረታች ውጤት ማስገኘቱን አስታውቀዋል፡፡