3ኛ ዙር የኦሮሚያ ባንክ ይቀበሉ ይመንዝሩ የሽልማት መርሃ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛ ዙር የኦሮሚያ ባንክ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ መርሀ ግብር የአንደኛ እጣ ባለ እድለኛ የአይሱዙ መኪና ተሸላሚ ሆነዋል ።
ኦሮሚያ ባንክ 3ኛው ዙር ይመዝሩ፣ ይቆጥቡ ፣ይሸለሙ መርሀ ግብር ለባለ እድለኞች ዛሬ ሽልማት አበርክቷል፡፡
በመርሃ ግብሩ የሀገርን ኢኮኖሚ ለመደገፍ ቀጥታ የተላከላቸውን ገንዘብ ከባንኩ የመነዘሩ ናቸው፡፡
የባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን÷ ሁሌም በባንክ ስርአት የምትመነዝሩ በውጭ ሀገር የምትኖሩ እና የባንኩ ደንበኞች ሀገርን እንደ ጠቀማችሁ እና እንደ ደገፋችሁ በማሰብ ከዚህ በኋላም ህገወጥ ምንዛሬን በመቃወም ለሀገር በአንድ መቆም አለብን ብለዋል።
ይህ የሽልማት መርሀ ግብር ከአራት ዲስትሪክት ከ73 በላይ እጣ በማዘጋጀት ዛሬ 36 የሚሆኑ ባለእድለኞች ሽልማት ተቀብለዋል፡፡
በዚህም አንደኛ እጣ አይሱዙ መኪና ፣ ሁለተኛ እጣ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ፣ ሶስተኛ እጣ የሞተር ሳይክል እንዲሁም አራተኛ እጣ የውሀ መሳብያ ሞተር፣ አምስተኛ እና ስድስተኛ እጣ ደግሞ ሶላር ባኔል እና የሞባይል ቀፎዎች መሆኑ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
በቅድስት ተስፋዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!