Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ሳይታገት “ታግቻለሁ” ብሎ በማስወራት ጥቅም ለማግኘት የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ሳይታገት “ታግቻለሁ” ብሎ በማስወራት የግል ጥቅም ለማግኘት የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጎንደር ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።
ወርቅነሀ ጎሸ የተባሉት ግለሰብ አርባባ አካባቢ ታግቻለሁ በሚል ለቤተሰቦቻቸው የደወሉ ሲሆን፥ የግል ተበዳይ የካቲት 2 ባለቤቴ ታግቷል የሚል ክስ ይዘው ወደ ጎንደር ከተማ አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ መጥተዋል።
የተበዳይ ክስ በመያዝ የወንጀል ምርመራውን ያደረገው ፖሊስ ጣቢያው ባደረገው ማጣራት ግለሰቡ በደባርቅ ከተማ ሆቴል ይዞ መገኘቱን አረጋግጧል።
ታጋቹ በተገኘበት ጊዜ ከሌሎች ግለሰቦች ጋር ካርታ እየተጫወተ የተያዘ ሲሆን፥ የሆቴሉን ባለቤት ጨምሮ ሌላ አንድ ግለሰብ በሰጡት ቃል መሠረት ግለሰቡ ብቻውን እንደመጣ እና በነፃነት ሲንቀሳቀስ እንደነበረ ተናግረዋል።
ምርመራው ገና በሂደት ላይ እንደሆነም የከተማው ፖሊስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል።
በኤልያስ አንሙት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.