ስፓርት

የጃንሜዳና 1ኛው የምሥራቅ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ውድድር በጃንሜዳ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

February 13, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የጃንሜዳና መጀመሪያው የምሥራቅ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ውድድር በጃንሜዳ እየተካሄደ ነው።

ከሩጫው መጀመር ቀደም ብሎ በኢፌዴሪ ባህልና ስፓርት ሚኒስትር የተዘጋጀው የማህበረሰብ አቀፉ የጤናና አካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተካሂዷል።

በጃንሜዳ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት እንቅስቃሴ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳም በሩጫ ውድድሩ ላይ መገኘታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!