በሀገር መከላከያ ሠራዊት ደቡብ ዕዝ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ማልበስ መርሃ- ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት ደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እና የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ የሠራዊት አባላት የሜዳሊያ የማዕረግ ማልበስ እና ሽልማት መርሃ ግብር ተካሄደ ።
የማዕረግ አሰጣጥ ሥነ-ስርዓት በመከላከያ ሰራዊት የብሄራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ኢተፋ ራጋን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በተገኙበት እየተከናወነ ነው።
የማዕረግ እድገቱ እየተሰጠ ያለው የዕዙ የላቀ የግዳጅ እፈፃፀም ላስመዘገቡ እና የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ የሠራዊት አባላት እንደሆነ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
የማዕረግ ዕድገቱ የባለ ሌላ ማዕረግ፥ መስመራዊ መኮንን እና ከፍተኛ መኮንን እንደሚያካትት ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።
የማዕረግ አሰጣጥ ሥነ-ስርዓቱ ለ33 የዕዙ አባላት ከምክትል አስር አለቃ እስከ ሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ የማልበስ ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!