Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ በኦሮሚያ ክልል ቆላማ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ8 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ልማት ማህበር በክልሉ ቆላማ አካባቢ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ 8ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነትና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የኦሮሚያ ልማት ማህበር ከፍተኛ ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ አልማ ፥ ድጋፉ በኦሮሚያ ቆላማ አካባቢዎች በድርቅ ለተጐዱ ዜጎች የሚውል መሆኑን ተናግረዋል።

የኦልማ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ ድጋፉ የመጀመሪያ መሆኑን ጠቁመው ፥ በተቻለ አቅም በሀገር አቀፍ ደረጃ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጐች ለመድረስ እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል።

በድጋፉ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዱ ኦልማ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው ፥ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልግ አካል በክልሉ አደጋ ስጋት ኮሚሽን በኩል ማድረግ እንደሚችል መግለጻቸውን ኤኤምኤን ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.