Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካና ብሪታኒያ ዛቻ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያላትን አቋም አይቀይረውም-ቭላድሚር ፑቲን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ እና ብሪታኒያ ዛቻ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያላትን አቋም አይቀይረውም ሲሉ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ፡፡
 
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የአሜሪካ አቻቸው ጆ ባይደን ከዩክሬን ጋር ተያይዞ በኔቶ አባል ሀገራት እና በሩሲያ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ዙሪያ በስልክ ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ የምታደርግ ከሆነ አሜሪካ እና አጋሮቿ ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጡ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስጠንቅቀዋል ፡፡
 
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው ÷ከፕሬዚዳንት ባይደን ጋር በሩሲያ እና በኔቶ አባል ሀገራት መካከል ባለው ውጥረት ሞስኮ ያቀረበቻቸውን ሃሳቦች ይገመግማሉ ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል፡፡
 
ይሁን እንጅ ሞስኮ በጉዳዩ ላይ ያሏት ቁልፍ ስጋቶች በውይይቱ ሊፈቱ እንደማይችሉ ነው ፕሬዚዳንቱ የገለጹት ፡፡
 
የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክትም ሆነ የኔቶ አባል አገራት ዛቻ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያላትን አቋም እንደማይቀይረውም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
 
እንደ ሩሲያው አርቲ ዘገባ÷60 ደቂቃ የወሰደው የሁለቱ ሃያላን አገራት መሪዎች የስልክ ውይይት ውጥረቱን ያረግበዋል ተብሎ ቢጠበቅም ምላሹ በተቃራኒው ሆኗል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.