Fana: At a Speed of Life!

5ሺህ ሰዎች የተገኙበት የፍቅር ምሳ ግብዣ በደሴ ከተማ አይጠየፍ አዳራሽ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሎ ሕዝብ በአንድነት የቀደመውን መልካም እሴት እንዲያስቀጥልና ደሴ ከተማ ያላትን ባህልና ወግ ይዛ እንድትዘልቅ ዓላማ ያደረገ 5 ሺህ ሰዎች የታደሙበት የፍቅር ምሳ ግብዣ በአይጠየፍ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
መርሃ ግብሩን የደሴ ከተማ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት አደራጅ ግብረ ኀይል እና በአዲስ አበባ የሚኖሩ የወሎ ባለሀብቶች በጋራ ያዘጋጁት ነው፡፡
በምሳ ግብዣው ላይ የሁሉም የሃይማኖት አባቶች፣ የደሴ ከተማ የሥራ ኀላፊዎችና ከሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.