የሀገር ውስጥ ዜና

የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኳታር ከሚገኙ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላትና የሐይማኖት አባቶች ጋር ተወያየ

By Meseret Awoke

February 14, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኳታር ዶሃ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላትና የሐይማኖት አባቶች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያየ።

ኑሯቸውን በኳታር ካደረጉ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የሃይማኖት ተቋማት አባቶች ጋር መወያየታቸውን የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀኃፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገልጸዋል። በውይይቱም ጉባኤው በኳታር ዶሃ ወደፊት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስለሚከፍትበት ሁኔታ ምክክር መካሄዱን ተናግረዋል።

በኳታር የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ከእምነት ተቋማት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ ስለሚያደርጉበት እንዲሁም ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሕብረተሰቡን ስለሚያግዙበት ሁኔታ ውይይት ተደርጓልም ነው ያሉት።

በሌላ በኩል አንዳንድ አካላት የወቅቱን አገራዊ ሁኔታ እንደጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ በሃይማኖቶች መካከል የፖለቲካ እና ሌሎች ልዩነቶችን በመፍጠር የሚያካሂዱትን ተግባር በተመለከተ ሰፊ ምክክር መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

በኳታር ዶሃ የጋራ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አደራጅ ኮሚቴ በመሰየምም ከግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም በኋላ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤቱ በይፋ እንደሚመሠረት መወሰኑን ጠቅላይ ጸሐፊው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!