በአማራ ክልል በጦርነቱ የወደሙ የልማት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚካሄደውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ ነኝ – ስዊድን
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊድን በአማራ ክልል በጦርነቱ የወደሙ የልማት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚካሄደውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች።
በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሀንስ ሄንሪክ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ጋር ዛሬ ባህርዳር ተገኝተው በወቅታዊ የክልሉ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።
በአምባሳደሩ የተመራውን የልዑካን ቡድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩት ዶክተር ይልቃል ከፋለ እንደገለጹት ፥ ክልሉ በአሸባሪው ህወሓት በተከፈተበት የግፍ ጦርነት ሳቢያ ከባድ የሰብዓዊና የመሰረተ-ልማት ውድመት ደርሶበታል።
ክልሉ አሁን ያለበትን አንፃራዊ ሰላም ተጠቅሞ ወደ መልሶ መቋቋም ልማት ስራ መግባቱን ዶክተር ይልቃል ጠቁመዋል።
የመልሶ መቋቋም ስራው የበርካታ አጋር አካላትን ድጋፍና ትብብር የሚጠይቅ መሆኑንም ገልጸዋል።
አምባሳደሩ የተደረገላቸው ማብራሪያ ክልሉ የደረሰበት ጉዳት ከባድ እና ዘርፈ ብዙ መሆኑን ለመገንዘብ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።
ስዊድንም በአማራ ክልል በጦርነቱ የወደሙ የልማት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚያካሄደውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አምባሳደሩ ማስታወቃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!