Fana: At a Speed of Life!

የንጹህ መጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የንጹህ መጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከውሃ ነክ ስራዎች ግንባታ ተቋራጭ ማህበር ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
ሚኒስቴሩ በስሩ የሚገነቡ የውሃ፣ የሳኒቴሽን እንዲሁም የኢነርጂ ፕሮጀክቶች ያሉባቸውን ክፍተቶች በማረም ለዜጎች አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ክልሎችን፣ ባለድርሻ ተቋማትን እንዲሁም የተቋራጭ ማህበራትን በተከታታይ ውይይት በማካሄድ አቅጣጫዎችን እየሰጠ ነው፡፡
የዋጋ ንረት፣ ያለ በቂ ምክንያት ውል ማቋረጥ፣ የመርከብ ትራንስፖርት ክፍያ ከፍተኛ መሆን፣ ከቀረጥ ነጻ ፈቃድ ሂደትን እንዲሁም ከሲሚንቶ እጥረት ጋር በተያያዘ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እየሰሩ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ተናግረዋል፡፡
በተለይም የሲሚንቶ አቅርቦትን በተመለከተ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር የተጀመረው ስራ በቅርቡ ውጤት ያስገኛል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.