Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው ዙር አገር አቀፍ የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ ተጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ዙር አገር አቀፍ የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት የሚካሄድ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደስ ገለጹ።

ሚንስትሯ የዘመቻውን መጀመር በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፥ በመጀመሪያው ዙር ዘመቻ ከ10 ሚልየን በላይ ዜጎች የኮቪድ-19 ክትባት ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በዛሬው እለት ሁለተኛው ዙር የክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል ያሉት ሚኒስትሯ፥ ለሁለተኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ ከ20 ሚልየን በላይ ክትባት መሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ በጤና ተቋማት እና ሰዎች በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች ጊዜያዊ ጣቢያ በማቋቋም ለሁለት ሳምንታት ክትባቱ ይሰጣል ነው የተባለው።

በዚህ ዘመቻ እድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የመጀመሪያ ክትባት ያልወሰዱ እንዲሁም የመጀመሪያውን ወስደው ሁለተኛውን ያልወሰዱ ዜጎች እንደሚከተቡ ኢዜአ ዘግቧል።

ለዘመቻው ስኬት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡና ዜጎችም እንዲከተቡ ሚንስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.