የሀገር ውስጥ ዜና

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳል

By Meseret Awoke

February 15, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያካሂደው አስቸኳይ ስብሰባ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ላይ ይመክራል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጨምሮ፣ የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅን፣ የግል ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እንዲሁም የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ነው ዛሬ ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ የወሰነው፡፡

የአዋጁ መነሳት በአዋጁ መደንገግ አጋጥሞ የነበረውን ምጣኔ ሃብታዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ ለመፍታት ሚናው የጎላ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ እና የአማካሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ታገሰ ጫፎ አብራርተዋል ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!