የሀገር ውስጥ ዜና

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እየተሰራ ያለው ስራ ውጤትማ መሆኑ ተመላከተ

By Meseret Awoke

February 15, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት ማምጣቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስ እና ጫማ ማቅረብ በመቻላችን ኩራት ይሰማናል ሲሉም ነው የኢንደስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የተናገሩት፡፡

ባለፉት ጊዜያት 1 ሚሊየን 55 ሺህ ጫማ ለጸጥታ ኃይሉ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ማስቀረት እንደተቻለ ገልጸው÷ ከ718 ሺህ በላይ ጫማዎችን ደግሞ ለተማሪዎች ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡

ከውጭ የሚመጡትን ምርቶች በሀገር ውስጥ ለመተካት እየተሰራ መሆኑን እና ሙሉ በሙሉ መተካት እንደሚቻልም ይህ አፈፃፀም ማሳያ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

በአልማዝ መኮንን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!