Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢንስቲትዩት ኃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በዛሬው እለት ከግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ እና የአውሮፓ ዳይሬክተር ዶክተር ማሌ ፎፎናን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚህ ወይይት ላይ ዶክተር ፍጹም ኢትዮጵያ በአለም አቀፍም ሆነ በአህጉርም ደረጃ የአረንጓዴ የኢኮኖሚ ልማት በግንባር ቀደምነት ስታቀነቅን መቆየቷን አስታውሰዋል፡፡
ከዚህ በፊትም በነበሩትም ሆነ የአስር ዓመቱ እቅድ አንዱ ምሰሶ አደጋ የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት መሆኑን ጠቁመው፥ በእቅድና ፖሊሲ ደረጃ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ኢኮኖሚ መገንባት ላይ ኢትዮጵያ አሁንም አጠናክራ መቀጠሏን ገልጸዋል፡፡
ይህንንም በሚደግፍ መልኩ አደረጃጀት መሻሻሉን አንስተው ፥ ሁሉም ዘርፎች የአየር ንብረት ለውጥና አካባቢ ጉዳይን አካተው እንዲያቅዱና እንዲፈጽሙ ተደርጓል ብለዋል ፡፡
ለአብነትም በትራንስፖርት፣ በውሃ እና ኢነርጂ፣ ኢንደስትሪ፣ በግብር እና ከተማ ልማት ዋንኞቹ መሆናቸውን ነው ያነሱት።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አነሳሽነት እየተተገበረ ያለው የአረንጓዴ አሻራ፣ የደን ሽፋንን ከመጨመር አኳያ ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ፍጹም አሰፋ እና ዶክተር ማሌ ፎፎና የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተሰጠው ኃላፊነት ላይ መሰረት በማድረግ የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥን የሚመለከቱ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢንስቲትዩት እ.አ.አ በ2012 የተመሠረተ ሲሆን፥ ከመሥራቾቹ መካከል ኢትዮጵያ ትገኝበታለች፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.