Fana: At a Speed of Life!

የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም በየሳምንቱ መጨረሻ በአዲስ አበባና ድሬዳዋ የተጀመሩትን አምራች እና ሸማችን በቀጥታ የማገናኘት ተግባር በሁሉም ክልሎች እንዲቀጥል እየተሰራ መሆኑን ነው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሃመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለፁት፡፡

ለዚህም የአሰራር ማእቀፍ በማዘጋጀት ደላላውን ከሰንሰለቱ ለማስወጣት ወደ ተግባር መገባቱን አብራርተዋል፡፡

በዋናነት የምርት ሁኔታን መጨመር እና የገበያ ሰንሰለትን ማሳጠርና ህገ ወጥ ግብይትን ተቆጣጣሪ ግብረ ሀይል እስከ ማቋቋም የደረሰ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡

የግብረ- ሀይሉ ቀዳሚ ስራ የዋጋ ንረቱን መቆጣጠር መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው ግብረ – ሀይሉ ከተቋቋመ በኋላ ሰው ሰራሽ ችግር ለመፍጠር ሲደክሙ በነበሩ ከ82 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ በቅጣት እንዲከፍሉ ተደርጓል ነው ያሉት ።

የመሰረታዊ ፍጆታን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ከውጭ ዘይት፣ ስንዴ፣ ስኳር መግባቱ ቀጥሏል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው÷ 4 ሚሊየን ኩንታል ስንዴና ከ10 ሚሊየን ሊትር በላይ ዘይት ገብቶ ወደ ክልሎች ስርጭት መጀመሩንም ተናግረዋል ።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ እንዳረጋገጡትም ÷መንግስት የኑሮ ውድነቱን ሸክሞች ተረድቷል ፤ የኢኮኖሚ አሻጥረኞችን በማስወገድ ምርትን በማሳደግና የገበያ ቅርበትን በየአከባቢው የማድረግ ስራ አጠናክሮ መስራቱን ይቀጥላል ብለዋል ።

በሀይለየሱስ መኮንን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.