Fana: At a Speed of Life!

ሁሉም ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ሀገራዊ አንድነት ሊሠራ ይገባል- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም የየራሱን አመለካከት ይዞ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ሀገራዊ አንድነት ሊሠራ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች እና ሰውነት ይቀድማል በጎ አድራጎት ማኅበር ጋር በመተባበር በደሴ ከተማ በሀገራዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እያካሄዱ ነው።

በምክክሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ኡለሞች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እንዳሉት፥ አንድነት እና ሰላምን በጋራ ማስጠበቅ ይገባል። ወሎ የእምነት አባቶች እና የኡለሞች መፍለቂያ መሆኗን ያወሱት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር÷ በተለይ በዚህ ወቅት መደጋገፍ እና መተባበር ያስፈልጋል ብለዋል።

የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ለዘመናት አብረው በአንድነት እና በመተባበር የኖሩ መሆኑን ያወሱት የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች ለሀገራቸው ዱዓ (ጸሎት) እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.