Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በማዳበሪያ ምርት ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራት ከሚፈልጉ ኩባንያዎች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስቴር በማዳበሪያ ምርት ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራት ከሚፈልጉ ኩባንያዎች አንዱ ከሆነው የቱርክ ኩባንያ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ባለሀብቶቹ በኢትዮጵያ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም የማዳበሪያ ፋብሪካ መገንባት የሚችሉበት ሁኔታ መነሳቱን ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል ።

በቅርብ ጊዜም ሌሎች ኩባንያዎችን በማወዳደር በማዳበሪያ ምርት ከመንግሥት ጋር በትብብር የሚሳተፉበትና የፋብሪካ ተከላ የሚያካሂዱበት ሂደት የሚጀመር መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.