የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ በማዳበሪያ ምርት ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራት ከሚፈልጉ ኩባንያዎች ጋር ተወያየ

By Feven Bishaw

February 15, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስቴር በማዳበሪያ ምርት ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራት ከሚፈልጉ ኩባንያዎች አንዱ ከሆነው የቱርክ ኩባንያ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ባለሀብቶቹ በኢትዮጵያ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም የማዳበሪያ ፋብሪካ መገንባት የሚችሉበት ሁኔታ መነሳቱን ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል ።