Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን ለመመከት በጋራ እንሰራለን-የሁለቱ አገራት የጸጥታ ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን በጋራ ለመመከት እንደሚሰሩ የሁለቱ አገራት የጸጥታ ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፤ የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት ኢንስፔክተር ጀነራል ሄላሪ ሙትያምባይ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቀሴ ለማረጋገጥ በጋራ የሚሰሯቸውን ሥራዎች ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በተለይም ደግሞ ኢትዮጵያና ኬንያ በጸጥታው ዘርፍ ተባብሮ በመሥራት በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የአሸባሪው ሸኔ እኩይ ተግባር ለማክሸፍ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

ኢንስፔክተር ጀነራል ሄላሪ ሙትያምባይ ፥ኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር አካባቢዎችን ጸጥታና ሰላም ለመጠበቅ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸው ሥምምነት ላይ ደርሰዋል ብለዋል።

የመረጃ ልውውጦችን በማሳደግና በማሻሻል በአካባቢው ያለውን ሰላም በጋራ እንጠብቃለንም ነው ያሉት።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን በጋራ ለመመከት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

በሁለቱ አገሮች አዋሳኝ አካባቢዎች የሸኔን እንዲሁም የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለማስቆም የጋራ ዘመቻ እናደርጋለን ብለዋል።

የጋራ ዘመቻው ወይም ኦፕሬሽን ውጤታማ እንዲሆን ከአንድ ወር ባጠረ ጊዜ ኬንያ ላይ የመግባቢያ ሥምምነት እንፈራረማለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.