Fana: At a Speed of Life!

የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ የሰራዊት አባላት እውቅና የመስጠት ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሚኒስቴር ምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ የሰራዊት አባላት እውቅና የመስጠት ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩም በመከላከያ ሚኒስቴር የሰራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ጀነራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።

በህግ ማስከበር፣ በህልውና እና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻዎች መሳካት የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የሰራዊቱ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም ክፍሎች የሚመሰገኑበት መሆኑን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በዚሁ መሠረት የሜዳይ፣ የማዕረግ እድገትና የምስክር ወረቀት እንደሚበረከትም ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.