Fana: At a Speed of Life!

የኢትጵያዊቷ አጊቱ ጉደታ ገዳይ የ20 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትሬንቶ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያዊቷ ሥራ ፈጣሪ አጊቱ ጉደታ ገዳይ በሆነው ሱሌማን አዳምስ ላይ የ20 ዓመት ጽኑ እስራት ፈርዶበታል፡፡

ፍርድ ቤቱ ትላንት የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ኢትዮጵያዊቷን ስራ ፈጣሪ አጊቱ ጉደታን ቤቷ ውስጥ በመዶሻ ጥቃት በማድረስ እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 29 ቀን 2020 ለህልፈተ ህይወት የዳረገው የ33 ዓመቱ ጋናዊ ሱሌማን አዳምስ ላይ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል።

አጊቱ በትሬንትኖ ሊጠፉ የተቃረቡ የፍየል ዝርያዎችን ከመጥፋት በመታደግና ውጤታማ ፍየል እርባታ፣ በአካባቢ እንክብካቤ፣ በወተትና ወተት ተዋፅኦ ምርት ውጤታማ የነበረች እና በጣሊያን ህዝብና መንግሰት እንዲሁም በዳያስፖራው ማህበረሰብ በአርአያነት ምትጠቀስ ነበረች።

ለዚህ ፍትህ መገኘት ቤተሰብ፣ የአካባቢው የመንግስት ኃላፊዎችና ነዋሪዎች እንዲሁም የትሬንቲኖ የኢትዮጵያ ዳያስፓራ ኮሚኒቲ ኤምባሲው ጋር በመስራት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን በሮም ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.